የሀገር ውስጥ ዜና

በኃይል ተገደው ወደ ጦርነት የገቡ ልዩ ኃይል አባላት ወደ አማራ ክልል በሰላማዊ መንገድ እየገቡ ነው

By Abrham Fekede

November 08, 2020

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 29፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በህወኃት ውስጥ ባለው ህገወጥና ዘራፊ ቡድን በኃይል ተገደው ወደ ጦርነት የገቡ የትግራይ ክልል ልዩ ኃይል አባላት ወደ አማራ ክልል በሰላማዊ መንገድ እየገቡ ነው፡፡

የልዩ ኃይል አባላቱ ከሃገር መከላከያ ሰራዊትና ከአማራ ክልል ልዩ ኃይል አባላት ጋር መዋጋታችን ትክክል አልነበረም ብለዋል፡፡ ይህንን በማመንም በሰላማዊ መንገድ ወደ አማራ ክልል ገብተናል ነው ያሉት፡፡