Fana: At a Speed of Life!

41 የሚሊሻ አባላት በህወሓት ውስጥ ባለ ቡድን የሚደርስባቸው ጫና በመቃወም አብርሃጂራ ከተማ ገቡ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 29፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በህወሓት ውስጥ ባለ ቡድን የሚደርስባቸው የሚደርስባቸውን አፈና እና እንግልት የተቃወሙ 41 የሚሊሻ አባላት ወደ አብርሃጂራ ከተማ ገቡ።
የሚሊሻ አባላቱ ነዋሪነታቸው በጸገዴ ወረዳ ሲሆን ወደ አማራ ክልል የገቡት በትግራይ ክልል ለሚገኘው በህወሀት ውስጥ ላለ ቡድን መጠቀሚያ ላለመሆን ነው ብለዋል።
በዚህ ቡድን ላይ መንግስት የጀመረውን ህግ የማስከበር እርምጃ በመደገፍና ከጸጥታ አካሉ ጋር በጋራ በመሆን የማገዝ ፍላጎቱ እንዳላቸውም ለአብመድ ተናግረዋል።
የትግራይ ህዝብም እንደ ሌሎቹ ወንድም ህዝቦች ነጻነቱን ማረጋገጥ እንዲችል ከፌዴራል መንግስት ጎን እንዲቆም መልዕክት አስተላልፈዋል።
በምዕራብ አርማጭሆ ወረዳ ወደ አብርሃጂራ ከተማ 41 የሚሊሻ አባላት እንደገቡም የምዕራብ ጎንደር ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ደሳለኝ ጣሰው ገልጸዋል።
በቀጣይም የልዩ ሃይል እና የሚሊሻ አባላት ቢገቡ ለመቀበል መዘጋጀታቸውን እና በሁለቱ ህዝቦች መካከል ያለውን አብሮነት አሁንም እንዲቀጥል እንደሚሰራ አስተዳዳሪው ተናግረዋል።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.