Fana: At a Speed of Life!

ተጨማሪ 474 ሰዎች ኮሮና ቫይረስ ሲገኝባቸው 818 ሰዎች ደግሞ አገግመዋል

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 29 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ ለ5 ሺህ 324 ሰዎች የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 474 ሰዎች ኮሮናቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።

ይህን ተከትሎም በኢትዮጵያ በአጠቃላይ ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 99 ሺህ 675 ደርሷል።

በሌላ በኩል ባለፉት 24 ሰኣት 818 ሰዎች ከቫይረሱ ሲያገግሙ በአጠቃላይም 59 ሺህ 766 ሰዎች ከቫይረሱ ማገገም ችለዋል።

ባለፉት 24 ሰዓታት በኮሮናቫይረስ የአምስት ሰዎች ህይወት ማለፉ መረጋገጡን ተከትሎ በቫይረሱ የሞቱ ሰዎች ቁጥር 1 ሺህ 523 ደርሷል።

በአሁኑ ወቅት ቫይረሱ ካለባቸው 38 ሺህ 384 ሰዎች መካከል 316 ያህሉ በጽኑ ሕክምና ላይ መሆናቸው ተገልጿል።

በኢትዮጵያ እስካዛሬ ድረስ በአጠቃላይ ለ1 ሚሊየን 526 ሺህ 221 ሰዎች የኮሮናቫይረስ የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጓል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.