Fana: At a Speed of Life!

በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 100 ሺህ ገደማ ደርሷል

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 30፣ 2013 (ኤፍቢሲ) በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ ከገባ ጀምሮ በወረርሽኙ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 100 ሺህ ገደማ ደርሷል፡፡

ወረርሽኙ ወደ ኢትዮጵያ መግባቱ የተሰማው ባለፈው ዓመት መጋቢት 3 ቀን እንደነበር የሚታወስ ሲሆን አሁን ላይ 99 ሺህ 982 ሰዎች በወረርሽኙ መያዛቸው ነው የተገለጸው፡፡

በወረርሽኙ የተያዙት ሰዎች ቁጥር ወደ 100 ሺህ መጠጋቱ የተሰማው ባለፉት 24 ሰዓታት የላቦራቶሪ ምርመራ ከተደረገላቸው 3 ሺህ 889 ሰዎች ውስጥ 307ቱ በቫይረሱ መያዛቸውን የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ በትዊተር መልዕክታቸው መግለጻቸውን ተከትሎ ነው፡፡

ሚኒስትሯ በትዊተር ገጻቸው ባሰፈሩት ፅሁፍ 290 ሰዎች በፅኑ ህክምና ላይ ይገኛሉ ብለዋል፡፡

በ24 ሰዓታት ውስጥ በቫይረሱ አማካኝነት ሰባት ሰዎች ህይወታቸውን አጥተዋል፡፡
በጥቅሉ በቫይረሱ አማካኝነት እስካሁን1 ሺህ 530 ህይወታቸውን ማጣታቸውን ገልጸዋል፡፡

ከዚህ ባለፈም 944 ሰዎች ከቫይረሱ ሲያገግሙ ይህን ተከትሎም ከቫይረሱ ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 60 ሺህ 710 ደርሷል፡፡

በአሁኑ ወቅት ቫይረሱ የሚገኝባቸው ሰዎች ደግሞ 37 ሺህ 740 ናቸው ተብሏል፡፡

ወረርሽኙ ኢትዮጵያ መግባቱ ከተሰማበት ዕለት ጀምሮ ለ1 ሚሊየን 530 ሺህ 110 ሰዎች የላብራቶሪ ምርመራ እንደተካሄደላቸው የሚኒስትሯ መረጃ ያመለክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.