የሀገር ውስጥ ዜና

በትግራይ ክልል እየተከናወነ የሚገኘው ህግን የማስከበር ስራ በታቀደው መንገድ እየሄደ ነው – ጠ/ሚ ዐቢይ

By Tibebu Kebede

November 10, 2020

አዲስ አበባ፣ ህዳር 1፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በትግራይ ክልል እየተከናወነ የሚገኘው ህግን የማስከበር ስራ በተቀመጠው እቅድ መሰረት እየተከናወነ መሆኑን አስታወቁ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በትዊተር ገጻቸው ባሰፈሩት ፅሁፍ ዘመቻው በህወሓት ውስጥ ያለው ጁንታ ትጥቅ ሲፈታና በክልሉ ተቀባይነት ያለው ህጋዊ አስተዳደር ሲመሰረት ዘመቻው እንደሚጠናቀቅም አስታውቀዋል፡፡

ከዚህ ባለፍም ችግር ፈጣሪዎች ለህግ ሲቀርቡ ዘመቻው በቅርቡ እንደሚጠናቀቅም ጠቅሰዋል፡፡