የበርሃ አንበጣ መንጋ የመከላከል ስራውን የሚያግዙ የእስራኤል ባለሙያዎች አዲስ አበባ ገቡ
አዲስ አበባ፣ ህዳር 1፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የበርሃ አንበጣ መንጋን በዘላቂነት መካላከል በሚቻልበት ዙሪያ ለኢትዮጵያ እገዛ የሚያደርጉ የእስራኤል ባለሙያዎች በዛሬው ዕለት አዲስ አበባ ገብተዋል።
ባለሙያዎቹ በኢትዮጵያ የበርሃ አንበጣ መንጋ ስርጭትን የመቆጣጠር ስራ ተሳትፎ የሚያደርጉ ናቸው ተብሏል።
ለቀጣዩ ሁለት ሳምንት በኢትዮጵያ ቆይታ የሚያደርጉት ባለሙያዎቹ ከ200 በላይ ለሚሆኑ ኢትዮጵያውያን ባለሙያዎች የበርሃ አንበጣ መከላከል መንገዶች ዙሪያ ስልጣና ይሰጣሉ ተብሏል።
የእስራኤል ምክትል የደህንነት ሚኒስትር ጋዲ ይቫርከን በኢትዮጵያ በነበራቸው ቆይታ የእስራኤል ባለሙያዎች ወደ ኢትዮጵያ እንደሚመጡ መዘገባችን የሚታወስ ነው።
ምክትል የደህንነት ሚኒስትሩ ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር በነበራቸው ቆይታ የበርሃ አንበጣ መከላከል ስራ ላይ ተጠምደው የሚገኙ ባለሙያዎችን ክህሎት ማሳደግ እንደሚገባ ተናግረዋል።