Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች በዓል የሕብረ-ብሔራዊ አንድነት ችቦ በጅግጅጋ ከተማ ተለኮሰ

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 1 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ዘንድሮ ለሚከበረው 15ኛው የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች በዓል የብሔር ብሔረሰቦች በዓል የሕብረ ብሔራዊ አንድነት ችቦ በዛሬው ዕለት በጅግጅጋ ከተማ ተለኩሷል።

በችቦ የመለኮስ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ አደም ፋራህ እና የግብርና ሚኒስትሩ አቶ ዑመር ሁሴን እንዲሁም የሶማሌ ክልል ምክትል ርእሰ መስተዳድር ሙስጠፌ ሙሐመድ እና ሌሎች የፌደራል እና የክልል ከፍተኛ ባለሥልጣናት ተገኝተዋል።

ዘንድሮ የሚከበረው የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦችን በዓል ምክንያት በማድረግ ከሚከናወኑ ክንውኖች መካከል አንዱ ከምሥራቅ ኢትዮጵያ ተነሥቶ በሁሉም ክልል የሚደርስ ሕብረ-ብሔራዊ አንድነት ችቦ ነው።

ችቦው ከሶማሌ ክልል ተነሥቶ በተለያዩ ክልሎች እና ከተማ መስተዳድሮች እንደሚዘዋወር ተገልጿል።

የዘንድሮው የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች በዓል “እኩልነት እና ሕብረ-ብሔራዊ አንድነት ለጋራ ብልጽግና” በሚል መሪ ቃል ለ15ኛ ጊዜ በፌዴሬሽን ምክር ቤት አስተባባሪነት እና በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስተናጋጅነት በአዲስ አበባ ከተማ እንደሚከበር ኢቢሲ ዘግቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.