Fana: At a Speed of Life!

የኦሮሚያ ልዩ ኃይል ከሌሎች የክልሉ የጸጥታ አካላት ጋር በመሆን የኦነግ ሸኔ ታጣቂ ቡድን ላይ እርምጃ እየወሰደ እንደሚገኝ ገለፀ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 1፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኦሮሚያ ልዩ ፖሊስ ኃይል ከሌሎች የክልሉ የጸጥታ አካላት ጋር በመሆን የኦነግ ሸኔ ታጣቂ ቡድን ላይ እርምጃ እየወሰደ እንደሚገኝ አስታወቀ።

ታጣቂ ቡድኑ የህዝብን ሠላም ለማደፍረስና ሕገመንግሥታዊ ሥርዓቱን በኃይል ለመናድ በተለያዩ የክልሉ አካባቢዎች እየተንቀሳቀሰ መሆኑንም አስታውቋል፡፡

ኮሚሽኑ እርምጃ በመውሰድ የሕግ የበላይነትን ለማስከበር እየሰራ መሆኑንም ገልጿል፡፡

ሰሞኑን በአንዳንድ የኦሮሚያ ዞኖች ባካሄደው ዘመቻ አንጸባራቂ ድል መመዝገቡን የክልሉን ፖሊስ ኮሚሽን ዋቢ ያደረገው የክልሉ ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ መረጃ ያመላክታል፡፡

የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን የኦነግ ሸኔ ኃይል ህዝብን የሚዘርፍ ሽፍታና ለጥፋት ተግባር እየተንቀሳቀሰ ያለ ቡድን ስለሆነ ህዝብ የዚህን እኩይ ቡድን ተግባር በመቃወምና ከጸጥታ አካላት ጎን በመቆም አጋርነቱን እንዲያሳይ ጥሪ አቅርቧል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.