Fana: At a Speed of Life!

የሶማሌ ክልል ም/ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌና የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ አደም ደም ለገሱ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 1፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የፌደራል፣ የሶማሌ ክልል ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች እና የጅግጅጋ ከተማ ነዋሪዎች በዛሬው ዕለት ደም ለግሰዋል።
በዚህም የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈጉባኤ አቶ አደም ፋራህ፣ የሶማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ ሙሀመድ እንዲሁም የክልሉ አመራሮች የደም ልገሳ አድርገዋል።
በጅግጅጋ ከተማ በተደረገው የደም ልገሳ ስነስርዓት በሰሜን እዝ ሀገርን ከጥፋት ለማዳን በግዳጅ ላይ የሚገኘው የሀገር መከላከያ ሠራዊት የሚውል የደም ልገሳ እንደሆነ መነገሩን ከሶማሌ ክልል ቴሌቪዥን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
በደም ልገሳ ስነስርዓቱም የክልሉ ህዝብ ከመከላከያ ሰራዊት ጎን በመቆም ሀገራቸውን እንዲጠብቁ ጥሪ ቀርቧል።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.