ዓለምአቀፋዊ ዜና

ሩሲያ ከድምፅ 27 እጥፍ የሚፈጥነውን ሀይፐርሶኒክ ሚሳኤል ወደ ስራ አስገባች

By Tibebu Kebede

December 28, 2019

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 18 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ሩሲያ  ከድምፅ 27 እጥፍ  የሚፈጥነውን አቫንጋር ሀይፐርሶኒክ ሚሳኤል ወደ ስራ ማስገባቷን የሀገሪቱ መከላከያ ሚኒስትር አስታወቀ፡፡

የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሜር ፑቲን ሚሳኤሉ ከድምፅ 27 አጥፍ በሚበልጥ ፍጥነት እንደሚጓዝ በመግለፅ ይህም ሩሲያን በዘርፉ ከአለም ቀዳሚዋ ያደርጋታል ብለዋል፡፡

ሚሳኤሉ መረጃ የሚያገኝበት ስርዓቱ በፍጥነት መንቀሳቀስ እንዲችል የሚያደርገው መሆኑ የተገለፀ ሲሆን ይህም ጥቃት እንዳይፈፀምበት የሚያስችል  መሆኑ ተጠቁሟል፡፡

የሩሲያ መከላከያ ሚኒስትር ሴርጄይ ሾጉ ሚሳኤሉ ወደ ስራ መግባቱን ያረጋገጡ ሲሆን ሁኔታን ፈር ቀዳጅ ሲሉ ገልፀውታል፡፡

ፕሬዚዳንት ፑቲን ሀይፐርሶኒክ ሚሳኤሉ የአሁን እና ወደፊቱ የሚሳኤል ስርዓት የቀደመ ብለውታል፡፡

ምዕራባውያን እና ሌሎች ሀገራትም ከዚህ ደረጃ ለመድረስ እየተንቀሳቀሱ መሆኑን ፕሬዚዳንቱ ገልፀዋል፡፡

ሚሳኤሉ በኡራልስ ተራራ አካባቢ ይቀመጣል ተብሎ የሚጠበቅ ፡፡

ምንጭ፡-ቢቢሲ