Fana: At a Speed of Life!

በፕሪምየር ሊጉ ወልቂጤ ፣ ጅማ አባ ጅፋርና ሲዳማ ቡና ተጋጣሚዎቻቸውን አሸንፈዋል

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 18 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ አምስተኛ ሳምንት በዛሬው ዕለት ስድስት ጨዋታዎችን በክልል ከተማዎች አስተናግዷል፡፡

በዚህም ወደ ጅማ ያቀናው ቅዱስ ጊዮርጊስ በጅማ አባ ጅፋር 2 ለ 1 ተሸንፏል፡፡

የጅማ አባ ጅፋርን የማሸነፊያ ግቦች ብዙዓየሁ እንደሻው በ13ኛው ደቂቃ እና አምረላ ደልታታ በ80ኛው ደቂቃ ላይ ሲያስቆጥሩ የጊዮርጊስን ብቸኛ ግብ ሄኖክ አዱኛ በ60ኛው ደቂቃ ላይ አስቆጥሯል፡፡

ሀዋሳ ከተማ ከሲዳማ ቡና ያደረጉት ጨዋታም በሲዳማ ቡና 3 ለ 1 አሸናፊነት ነው የተጠናቀቀው፡፡

ለሲዳማ ቡና አማኑኤል እንዳለ በ12ኛው ፣ ሀብታሙ ገዛህኝ 55ኛው እና ይገዙ ቦጋለ በ64ኛው ደቂዎች ላይ ሲያስቆጥሩ የሀዋሳ ከተማን ግብ ብሩክ በየነ ማስቆጠር ችሏል፡፡

ወላይታ ድቻ ዘንድሮ ፕሪምየር ሊጉን የተቀላቀለውን ወልቂጤ ከተማ አስተናግዶ 1 ለ 0 በሆነ ውጤት የተሸነፈ ሲሆን የክትፎዎቹን የማሸነፊያ ግብ ጫላ ተሺታ 41ኛው ደቂቃ ላይ አስቆጥሯል፡፡

በሌሎች ጨዋታዎች ባህርዳር ከነማ ከሆስዕና ከተማ 2 ለ 2 ፣ ስሑል ሽረ ከአደማ ከተማ 1 ለ 1 እንዲሁም ድሬደዋ ላይ ድሬደዋ ከተማ ከኢትዮጵያ ቡና 0 ለ 0 በሆነ አቻ ውጤት ተለያይተዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.