Fana: At a Speed of Life!

የድንጋይ ከሰልን በዘመናዊ መንገድ ለማምረት የአዋጭነት፣ የጂኦሎጂ ምርመራና የቦታና የክምችት መጠን የሚለይ ቡድን ተቋቋመ

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 2 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የድንጋይ ከሰልን በዘመናዊ መንገድ ለማምረት የአዋጭነት፣ የጂኦሎጂ ምርመራና የቦታና የክምችት መጠን የሚለይ ቡድን መቋቋሙን የማዕድንና ነዳጅ ሚኒስትር ኢንጅነር ታከለ ኡማ አስታወቁ።

በመሆኑም የተቋቋመው ቡድን ያገኛቸውን ወጤቶች ለብሔራዊ ኮሚቴ የሚያቀርብ ሲሆን ስራ መጀመሩም ተጠቁሟል።

ሚኒስትሩ በሀገሪቱ ከፍተኛ የድንጋይ ከሰል ክምችት ቢኖርም የዚህ ሀብት መኖር ግን ኢትዮጵያን ከወጪ እንዳልታደጋት ገልፀዋል።

በዚህም በዓመት ለድንጋይ ከሰል ግዢ ብቻ 227 ሚሊየን ዶላር ኢትዮጵያ ወጪ እንደምታርግ የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።

ይህም በኦሮሚያ፣ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ እና በደቡብ ክልሎች በስፋት የሚገኘውን የድንጋይ ከሰል ለሲሚንቶ፣ ለብረታብረት እና ለጨርቃጨርቅ ፋብሪካ ግብዓት በሙሉ አቅም ለማቅረብ ይረዳል ነው የተባለው።

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.