Fana: At a Speed of Life!

አዲሱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሥራቸውን ጀመሩ

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 2 ፣2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና አዲሱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ስራቸውን በይፋ ጀመሩ፡፡

ሚኒስትሩ በዛሬው እለት ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ጋር በመስሪያ ቤቱ በመገኘት ትውውቅ አድርገዋል፡፡

በዚህ ወቅትም የስራ ሃላፊዎቹ ዝርዝር የስራ ሂደታቸውን በተመለከተ ለሚኒስትሩ ገለጻ አድርውላቸዋል፡፡

ተሰናባቹ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ገዱ አንዳርጋቸውም ለአዲሱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የተሳካና መልካም የስራ ዘመን እንደተመኙላቸው ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

አቶ ገዱ አንዳርጋቸው በቅርቡ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የደህንነት አማካሪ ሆነው መሾማቸው ይታወሳል፡፡

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.