Fana: At a Speed of Life!

በአፋር ክልል የህወሓት ቡድን በሀገር መከላከያ ሰራዊት ላይ ያደረሰውን ጥቃት የሚያወግዝ ሰልፍ ተካሄደ

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 3 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በአፋር ክልል የህወሓት ቡድን በሀገር መከላከያ ሰራዊት ላይ ያደረሰውን ጥቃት የሚያወግዝ ሰልፍ ተካሄደ።

የህወሓት ቡድን በሀገር መከላከያ ሰራዊት በተለይም በሰሜን ዕዝ ላይ ያደረሰውን ክህደትና ጥቃት በመቃወም የሰመራ ሎጊያ አካባቢዋ ነዋሪዎች የተቃውሞ ሰልፍ አካሄደዋል፡፡

በሰልፉ መንግስት የጀመረውን ህግ የማስከበር ተግባር አጠናክሮ መቀጠል እንዳለበትና ህዝቡም ከሀገር መከላከያ ሰራዊት ጎን እንደሚቆም ገልፀዋል።

ሰልፈኞቹ የህወሓት ቡድን በመከላከያ ሰራዊት ላይ ያደረሰውን ጥቃት የተለያዩ መፈክሮችን በመያዝ አውግዘዋል፡፡

በሰልፉ ላይ ለመከላከያ ሰራዊቱ ያላቸውን አጋርነት መግለጻቸውንም ከአፋር ብሄራዊ ክልል ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.