ቢዝነስ

አየር መንገዱ የኮቪድ-19 ክትባትን ለማጓጓዝና ለማሰራጨት 21 አውሮፕላኖችን አዘጋጀ

By Feven Bishaw

November 12, 2020

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 3 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ የኮቪድ-19 ክትባትን ለማጓጓዝና ለማሰራጨት 21 አውሮፕላኖችን ማዘጋጀቱን ገለጸ።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የካርጎና ሎጂስቲክ አገልግሎት ማኔጂንግ ዳይሬክተር አቶ ፍጹም አባዲ እንደገለጹት÷ የኮቪድ-19 ክትባትን ለማከማቸት የሚያስችል መሰረተ ልማት ተሟልቷል።

ማጓጓዙን እና ማሰራጨቱን ስኬታማ ለማድረግም አሰራር መነደፉን ተናግረዋል፡፡

የተዘጋጁት 21 አውሮፕላኖችም የክትባቱን ደህንነት በአግባቡ የሚጠብቁ መሆናቸውን ዳይሬክተሩ ማመላከታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከዚህ ቀደም የኮቪድ-19 መከላከያ ቁሳቁስ በማሰራጨት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማበርከቱ ይታወቃል።