ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ ብራይት ስታር የበጎ አድራጎት ድርጅትን ጎበኙ
አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 19፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ በአዲስ አበባ ሽሮ ሜዳ አካባቢ የሚገኘውን ብራይት ስታር የበጎ አድራጎት ድርጅትን ጎበኙ።
በጉብኝቱ ላይ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢህ አህመድ በተጨማሪ ሌሎች የሚኒስትሮች ምክር ቤት አባላትም ተሳትፈዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ ጉብኝቱን አስመልክተው በፌስቡክ ገጻቸው ባወጡት መረጃም፥ “ዛሬ ከሰዓት በኋላ ብራይት ስታር ኢትዮጵያ የተሰኘውን ጉብኝት ስላዘጋጁ የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትርን ለማመስገን እወዳለሁ” ብለዋል።
እስከ 200 የሚደርሱ በጎዳና ላይ የሚኖሩና ለችግር የተጋለጡ ህፃናት ቀጣይ ህይወት ለመደገፍ የተደራጀውን የማእከሉን እንቅስቃሴዎች ከሚኒስትሮች ምክር ቤት አባላት ጋር በመሆን መጎብኘታቸውንም ገልፀዋል።
በዚያውም ትርፍ ጊዜያቸውን በበጎ አድራጎትና በተመሳሳይ ሰብአዊ ስራዎች ለሚያሳልፋት ዶክተርር አሚር አማን ሽኝት መደረጉንም ነው ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ ያስታወቁት።
በዚሁ ወቅትም ዶክተር አሚር አማን የተዘጋጀላቸውን ስጦታም ከጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ እጅም ተቀብንለዋል።
“ነፃ ጊዜያችንን ተጋላጭ ማህበረሰቦችን ለመደገፍ እና ለእድገታቸው አስተዋፅኦ ለማድረግ ማዋል ክቡር ብቻ ሳይሆን የመልካም ዜግነት ምልክትም ነው” ሲሉም ጠቅላይ ሚኒስትሩ መልእክት አስተላልፈዋል።