አቶ ደመቀ መኮንን ከደቡብ አፍሪካ ዓለም አቀፍ ግንኙነትና ትብብር ሚኒስትር ጋር በስልክ ተወያዩ
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 3፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ከደቡብ አፍሪካ ዓለም አቀፍ ግንኙነትና ትብብር ሚኒስትር ናሌዲ ፓንዶር ጋር በስልክ ተወያዩ።
በውይይቱም በኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ መምከራቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።
በውይይቱም ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን፥ በኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ እና የፌደራሉ መንግስት በትግራይ ክልል እያከሄደ ባለው ህግ የማስከበርና የህልውና ዘመቻ ላይ ማብራሪያ ሰጥተዋል።
የኢትዮጵያ መንግስት በትግራይ ክልል እያደረገ ያለው ተግባር የህግ የበላይነትን የማስከበር መሆኑንም ገልፀዋል።
በዚህም መንግስት በትግራይ ክልል ያለውን ህገ ወጡን የህወሓት ቡድን ለህግ ማቅረብ መሆኑን አንስተዋል።
አያይዘውም በትግራይ እየተካሄደ ያለው ዘመቻ ህገ ወጡ የህወሓት ቡድን በህግ ቁጥጥር ስር ሲውል ፍፃሜውን የሚያገኝ መሆኑንም አስታውቀዋል።
ወይዘሮ ናለዲ ፓንዶር በበኩላቸው÷ ደቡብ አፍሪካ የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኔታ በቅርበት እየተከታተለች መሆኑን ገልጸዋል፡፡
አያይዘውም የኢትዮጵያ መንግስት በትግራይ ስራውን ሲያከናውንም የዜጎችን ደህንነት እንደሚያረጋግጥ ያላቸውን እምነት ገልጸዋል ፡፡
ሚኒስትሯ አቶ ደመቀ በቅርቡ የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆነው በመሾሞ እንኳን ደስ አሎት ብለዋል።
#FBC
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።