Fana: At a Speed of Life!

በኦሮሚያ በ13 ከተሞችና በ11 ዞኖች ፅንፈኛውን የህወሓት ቡድንን የሚያወግዙ ሰልፎች ተካሄዱ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 4፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኦሮሚያ ክልል በዛሬው ዕለት 13 ትላልቅ ከተሞች እና በ11 ዞኖች የተለያዩ ወረዳዎች ፅንፈኛውን የህወሓት ቡድንን የሚያወግዙ ሰልፎች ተካሂደዋል።

በሰልፎቹ ላይ የተሳተፉ የክልሉ ነዋሪዎች ለሀገር የመከላከያ ሰራዊት ያላቸውን ድጋፍ መግለፃቸውንም በኦሮሚያ ክልል ምክተል ርእሰ መስተዳድት ማእረግ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪ አቶ አዲሱ አረጋ አስታውቀዋል።

ሰልፎቹም በነቀምቴ፣ ሰበታ፣ ቡራዩ፣ ሆለታ፣ ሱሉልታ፣ ለገጣፎ ለገዳዲ፣ ብሾፍቱ፣ ሞጆ ፣ አዳማ ፣ሻሸመኔ፣ ባቱ፣ ሮቤ   ከተሞች ተካሂደዋል።

እንዲሁም ሰልፍ የተካሄደባቸው ዞኖች ደግሞ ምስራቅ ወለጋ፣ ቦረና፣ ምዕራብ አርሲ፣ ባሌ፣ ምዕራብ ሀረርጌ፣ ጉጂ፣ ምስራቅ ሸዋ፣ ኢሉአባቦር፣ የፊነፊኔ ዙሪያ የኦሮሚያ ልዩ ዞን፣  ምዕራብ ጉጂ እና ሰሜን ሸዋ መሆናቸውንም አስታውቀዋል።

በሰልፉ ላይ የተሳተፉ የህብረተሰብ ክፍሎችም የተለያዩ መፈክሮችን ያሰሙ ሲሆን ከእነዚህም መካከል፥ “ስግብግቡ የህወሓት ጁንታ የፈጸመውን ሀገራዊ ክህደት እናወግዛለን፤ ህወሓትና ኦነግ ሸኔ ተቀናጅተው ሀገር ለማስፈርስ የሚንቀሳቀሱ ከሃዲ የህዝብ ጠላት ናቸው፤  መንግሥት የህግ የበላይነትን ለማስከበር እየወሰደ በለው እርመጃ ሁለንታዊ ድጋፍ እናደርጋለን” የሚል ይገኝበታል።

እንዲሁም “የሉዓላዊነታችን ጋሻና መከታ የሆነውን ጀግና መከላከያ ሠረታዊታችንን በሙሉ አቅማችን ከጎኑ እንቆማለን፤ የህዝቦችን አንድነት በማጠናከር የህወሓትና የኦነግ ሸኔ አፍራሽ ሴራን እናጋልጣለን፤ ሀገራዊ ለውጣችን በከሃዲዎች ሴራ አይደናቀፍም” የሚሉ መፈክሮችም ይገኙበታል።

በሁሉም ከተሞች እና ዞኖች የተካሄዱት ሰልፎች በሰላም መጠናቀቃቸውን ያስታወቁት አቶ አዲሱ፥ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችም ለመከላከያ ሰራዊት የተለያዩ ድጋፎችን በአይነት እና በገንዘብ በመስጠት ላይ እንደሚገኙም ገልፀዋል።

በኦሮሚያ ክልል በሚገኙ አስር የደም ባኮችም  “ደማችን ለመከላከያችን !” በሚል መሪ ቃል የደም ልገሳዉ ተጠናክሮ መቀጠሉንም አስታውቀዋል።

#FBC

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ፦ https://t.me/fanatelevision

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.