Fana: At a Speed of Life!

የሰብዓዊ መብት ጥሰጥ የሚፈጽሙ የፖሊስ አባላት ላይ እርምጃ መወሰዱ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ህዳር 4 ፣2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የሰብዓዊ መብት ጥሰጥ የሚፈጽሙ የፖሊስ አባላት ላይ እርምጃ መወሰዱ ተገለጸ፡፡

በእሰረኛ አያያዝና ምርመራ ወቅት በሰዎች ላይ ድብደባና አግባብበት የሌለው ተግባራትን የፈጸሙ የፖሊስ አባላት ከስራ ገበታቸው እንዲታገዱና በህግ እንዲጠየቁ የማድረግ ስራ እየተሰራ ነው ተባለ፡፡

በየካ ክፍለ ከተማ የማህበረሰብ አቀፍ የፖሊስ አገልግሎት መምሪያ ኮማንደር ባሳዝነው አክሎክ እንደገለጹት ሁለት የፖሊስ አባላቶች በፈጸሙት የሰብዓዊ መብት ጥሰት እርምጃ ተወስዶባቸዋል ብለዋል፡፡

በቀጣይም መሰል ያልተገባ ድርጊት በሚፈጽሙ የፖሊስ አካላት ላይ ክትትል በማድረግ የሚወሰደው እርምጃን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልጸዋል፡፡

ከጠቅላይ አቃቤ ህግ ያገኘነው መረጃ እንደሚያሳየው በቦሌና የካ ፖሊስ መምሪያዎች ከወቅታዊ ሁኔታ ጋር ተያይዞ የፖሊስ አባላትን ጨምሮ በርካታ ተጠርጣሪዎች ተይዘው ምርመራ እየተደረገባቸው መሆኑ ተገልጿል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.