አቶ ደመቀ መኮንን በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ መቀመጫቸውን አዲስ አበባ ላደረጉ አምባሳደሮችና ዲፕሎማቶች ማብራሪያ ሰጡ
አዲስ አበባ፣ ህዳር 4፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ መቀመጫቸውን አዲስ አበባ ላደረጉ አምባሳደሮችና ዲፕሎማቶች ማብራሪያ ሰጡ፡፡
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩማብራሪያ የሰጡት በትግራይ ክልል አሁን ላይ እየተከናወነ ያለውን የህግ ማስከበር ስራ አስመልክቶ መሆኑ ነው የተገለጸው።
በማብራሪያቸው ይህ ህግን የማስከበር ስራ ኢላማ ያደረገው ህግ የጣሱ ግለሰቦችን እንጂ ሰላማዊ ዜጎችን አለመሆኑን ለዲፕሎማቶቹ አብራርተዋል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ይህን የህግ ማስከበር ስራ አጠር ባለ ጊዜ ውስጥ ለማከናወን እየተሰራ ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።