የሀገር ውስጥ ዜና

ትናንት ምሽት ወደ ባሕርዳር እና ጎንደር ሮኬት መተኮሱን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መረጃ ማጣሪያ አስታወቀ

By Tibebu Kebede

November 14, 2020

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 5፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ትናንት ምሽት ወደ ባሕርዳር እና ጎንደር ሮኬት መተኮሱን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መረጃ ማጣሪያ አስታወቀ፡፡

በዚህም በአውሮፕላን ማረፊያው አካባቢ መጠነኛ ጉዳት ደርሷል ብሏል።

ስግብግቡ ጁንታ በእጁ ያሉትን የመጨረሻዎቹን መሣሪያዎች ጠጋግኖ ለጥፋት ተልዕኮ ለማዋል ሞክሯል ሲልም ነው ያስታወቀው፡፡

ይህም ከመሞቱ በፊት የመጨረሻውን ዐቅሙን እየሞከረ መሆኑን ያመለክታል ነው ያለው።

ዝርዝሩን መርማሪ ቡድን በሰፍራው ተመድቦ እያጣራው መሆኑንም የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መረጃ ማጣሪያ ገልጿል፡፡