Fana: At a Speed of Life!

የብሔራዊ የአደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን አሰራር ማሻሻያ ቴክኒካል ኮሚቴ ተዋቀረ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 5፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የብሔራዊ የአደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን አሰራር ማሻሻያ (ሪፎርም) ላይ የሚሰራ የቴክኒካል ኮሚቴ ተዋቀረ፡፡

ኮሚቴው በሰላም ሚኒስቴር ሰብሳቢነት ነው የተዋቀረው።

የኮሚቴው አላማ በዋነኛነት ኮሚሽኑ ማንኛውም ተፈጥሯዊ አደጋ ከመድረሱ በፊት የዝግጁነት ስራ ላይ ማተኮር እንዲቻል ፖሊሲ እና መመሪያ ቀርጾ በተያዘለት የጊዜ ሰሌዳ ወደ ስራ ማስገባት መሆኑን ሚኒስቴሩ ገልጿል።

የሰላም ሚኒስትር ወይዘሮ ሙፈሪሃት ካሚል ኢትዮጵያ ከእድገቷ አኳያ የአደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ላይ በጥልቀት ሊሰራበት እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡

አዲስ ለተዋቀረው ቴክኒካል ኮሚቴም የስራ አቅጣጫ አስቀምጠዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.