በባህር ዳር መኮድ እና በጎንደር አዘዞ የደረሰው መለስተኛ ፍንዳታ በቁጥጥር ውሏል
አዲስ አበባ፣ ህዳር 5፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ምሽት 5:00 ሰዐት ገደማ በባህር ዳር መኮድ እና በጎንደር አዘዞ አካባቢ መለስተኛ ፍንዳታ እንደተፈፀመ እና በቁጥጥር ስር መዋሉን የአማራ ክልል መንግስት አስታወቀ፡፡
የክልሉ መንግስት የጠላት ኃይል ሙሉ አቅሙን ተጠቅሞ የሽብር ስራ እየሰራ ስለሆነ ህብረተሰቡ ተረጋግቶ እራሱንና አካባቢውን በንቃት እንዲጠብቅ አሳስቧል፡፡
በአካባቢው የተከሰቱ ፍንዳታዎች ቢኖሩም ፍንዳታው በጸጥታ ኃይሉ በትንሽ ደቂቃዎች ውስጥ በቁጥጥር ስር ውሏል ብሏል፡፡
ከዚህ ጋር ተያይዞ በሁለቱም ከተማዎች የተለየ የመብራት መቆራረጥ አልተፈጠረም ተብሏል፡፡
መንግስት ከተሞቹ በሰላማዊ ሁኔታ ውስጥ ይገኛሉም ነው ያለው፡፡