Fana: At a Speed of Life!

የሲዳማ ክልል የስፖርት ምክር ቤት የምሥረታ ጉባዔ ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 5፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የስፖርት ምክር ቤት የምሥረታ ጉባዔ ተካሄደ።

በጉባዔው ላይ የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ የመንግሥት ሥራ ኃላፊዎች፣ የወረዳና ከተማ አስተዳደር ዋና አስተዳዳሪዎች እንዲሁም የተለያዩ ስፖርት ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንቶችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል ።

የምክር ቤቱ የመመሥረቻ ደንብና የ2013 በጀት ዓመት ዕቅድ ቀርቦ በምክር ቤቱ አባላት ውይይት ተደርጎ ውሳኔ እንደሚተላለፍ ከክልሉ ባህል ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.