Fana: At a Speed of Life!

መከላከያ ሠራዊትና የክልሉ የጸጥታ አካላት በድባጤ ወረዳ የተለያዩ አካባቢዎች በጸረ-ሠላም ኃይል ላይ በወሰዱት እርምጃ በርካታ የጸረ ሰላም ሀይሎች ተደመሰሱ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 5፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) መከላከያ ሠራዊትና የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የጸጥታ አካላት በድባጤ ወረዳ የተለያዩ አካባቢዎች ጥቃት ለማድረስ በገባው ጸረ-ሠላም ኃይል ላይ በወሰዱት እርምጃ በርካታ የጸረ ሠላም ኃይሎች መደምሰሳቸው ተገለጸ።
በድባጤ ወረዳ የተለያዩ አካባቢዎች በተወሰደው እርምጃ ከተደመሰሱት የጸረ-ሠላም ኃይሎች በተጨማሪ በርካቶች መማረካቸውም ነው የተነገረው።
በትናንትው እለትም በሕወሓት የሚደገፈው የጥፋት ቡድን በመተከል ዞን ድባጤ ወረዳ ባደረሰው ጥቃት የንጹኃን ዜጎች ዜጎች ሕይወት ማለፉም ተገልጿል።
የጸጥታ አካላት በቦታው ደርሰው በቡድኑ ላይ በወሰዱት እርምጃ በጥቃቱ የከፋ ጉዳት ሳይደርስ ማብረድ መቻሉም ተመላክቷል።
ግብዓተ-መሬቱ የተቃረበው ጽንፈኛው ሕወሓት እየተንገዳገደ ባለበት በዚህ ወቅት ዘግናኝ ጥፋቶችን ከመፈጸም ወደ ኋላ እንደማይል እያሳየ ቢሆንም ይህ ደግሞ የበለጠ የሚያጠንክረን ይሆናልም ነው የተባለው።
መንግስት ሕዝቡ በተቀናጀ መንገድ በመቆም ይህ አረመኔ ኃይል ለአንዴናን ለመጨረሻ ጊዜ እንዲወገድ በጽኑ ይሠራሉ ተብሏል።
የክልሉ መንግስት በመተለይም በመተከል ዞን ያለውን የጸጥታ ችግር በዘላቂነት ለመፍታት በትኩረት እየሠራ መሆኑ ተገልጿል።
በመሆኑም ህብረተሰቡ ከመቼውም ጊዜ በላይ በተደራጀ መንገድ ከመከላከያ ሠራዊትና ከክልሉ የጸጥታ አካላት ጎን በመቆም ለአካባቢያችሁ ሠላም የበኩላችሁን እንድትወጡ ሲል የክልሉ መንግስት ጥሪማቅረቡን ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.