በኢትዮጵያ ተጨማሪ 564 ሰዎች ኮሮና ቫይረስ ሲገኝባቸው 104 ሰዎች ደግሞ አገግመዋል
አዲስ አበባ፣ህዳር 5፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ በተደረገ 6 ሺህ 343 የላቦራቶሪ ምርመራ 564 ሰዎች ኮሮናቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።
ይህን ተከትሎም በኢትዮጵያ በአጠቃላይ ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 102 ሺህ 321 ደርሷል።
በሌላ በኩል ባለፉት 24 ሰዓታት የ7 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ በዚህም ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር 1 ሺህ 565 ደርሷል።
በሌላ በኩል የዛሬውን ጨምሮ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 63 ሺህ 675 መድረሱ ተመላክቷል።
በአሁኑ ወቅት ቫይረሱ ካለባቸው 37 ሺህ 79 ሰዎች መካከል 321 ያህሉ በጽኑ ሕክምና ላይ መሆናቸው ተገልጿል።
በአገሪቱ እስካዛሬ ድረስ በአጠቃላይ ለ1 ሚሊየን 557 ሺህ 6 ሰዎች የኮሮናቫይረስ የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጓል።
#FBC
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።