Fana: At a Speed of Life!

ግድቡ የብርቱ ህዝቦች የአንድነታችን ፣የአብሮነታችን ማሳያ የብልጽናችን መሰረት በመሆኑ እንደ ህወሓት አይነት ባንዳዎች ከፍጻሜው ለአፍታም አያስቆሙንም- ወ/ሮ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ፣ህዳር 6፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ለታላቁ የህዳሴ ግድብ ግንባታ ከ313 ሚሊየን ብር በላይ ተሰብስቧል፡፡
ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ዋንጫን ከአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ለየካ ክፍለ ከተማ አስረክበዋል ።
በዋንጫ ርክክቡ ወቅት ምክትል ከንቲባዋ እንደገለፁት ÷እስካሁን በተለያዩ ክፍለ ከተሞች ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ እየተደረጉ ያሉ ድጋፎች ከታቀደው በላይ መሆኑን ገልጸዋል ።
ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የብርቱ ህዝቦች የአንድነታችን ፣የአብሮነታችን ማሳያ እና የብልጽናችን መሠረት በመሆኑ እንደ ህወሓት አይነት ባንዳዎች ከግድቡ ፍጻሜ ለአፍታም አያስቆሙንም ሲሉ ተናግረዋል ።
የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ይታያል ደጀኔ በበኩላቸው ÷በሁለት ሳምንት ጊዜ ውስጥ ለግድቡ ግንባታ ከ313 ሚሊየን ብር በላይ በቦንድ ግዥና በስጦታ መሰብሰቡን ገልጸዋል ።
ዋንጫው በክፍለ ከተማው ቆይታ በሚያደርግበት ቀናት በመከላከያ ሰራዊቱ ላይ የደረሰው ክህደት አስደንጋጭ ቢሆንም ህብረተሰቡ ለበለጠ እልህና ቁጭት በመነሳሳት ለሃገር አለኝታነቱን አረጋግጧል ብለዋል ።
በተጨማሪም ስለህዳሴ ግድብ ፍትሀዊ ተጠቃሚነት በተለያዩ አለምአቀፍ ሚዲያዎች ድምጹን ሲያሰማ ለነበረው መሀመድ አል-አሩሲ የእውቅና ሽልማት ከምክትል ከንቲባ ወይሮ አዳነች አቤቤ እንደተበረከተላቸው ከአዲስ አበባ ከተማ ፕሬስ ሴክሬቴሪያት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.