Fana: At a Speed of Life!

ህዝቡ ለመከላከያ ሰራዊት አያደረገ ያለው ድጋፍ ለሀገሩና ለሰራዊቱ ያለውን ክብርና ፍቅር የሚያሳይ ነው- ዶ/ር ቀናዓ ያደታ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 6፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ህዝቡ ለመከላከያ ሰራዊት አያደረገ ያለው ድጋፍ ለሀገሩና ለሰራዊቱ ያለውን ክብርና ፍቅር የሚያሳይ መሆኑን የኢፌዴሪ የመከላከያ ሚኒስትር ዶክተር ቀነዓ ያደታ ገለፁ።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሚንስተር ዶክተር ቀናዓ ያደታ፣ የጅማ ዞን እና የጅማ ከተማ ነዋሪዎች ለሀገር መከላከያ ሰራዊት ያበረከቱትን ድጋፍ ተረክበዋል።

በስነ ስርዓቱ ላይም የሰላም ሚኒስትር ደኤታ ወይዘሮ ፍሬዓለም ሽባባው እና የመከላከያ ኢንዶክትሪኔሽን ዋና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ሜጀር ጀነራል መሀመድ ተሰማን ጨምሮ ሌሎችን የፌደራል እና የክልል የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

የጅማ ዞን ነዋሪዎች ፅንፈኛው የህወሓት ቡድን በሰሜን እዝ የመከላከያ ሰራዊት ላይ የፈፀመውን ክህደት በማውገዝ ለመከላከያ ስራዊት 515 ሰንጋዎችን፣ 414 በግና 300 ኪሎ ግራም ማር በአጠቃላይ 15 ሚሊየን ብር የሚገመት ድጋፍ አድርጓል።

በተመሳሳይ የጅማ ከተማ ነዋሪዎች ለኢፌዴሪ የሀገር መከላከያ ሰራዊት በገንዘብና በአይነት ከ8 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት ድጋፍ አድርገዋል።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሚኒስቴር ሚንስትር ዶክተር ቀነዓ ያደታ ለመከላከያ ሰራዊት ድጋፍ ያደረጉት ለዞኑና ለከተማው ነዋሪዎች ምስጋና አቅርበዋል።

የሀገርን ዳር ድንበር እና ሰላም ለመጠበቅ ዘብ በቆሙት የሰሜን እዝ አባላት ላይ በባንዳው ህወሃት የተፈፀመው ክህደት አሳፋሪ ነው ብለዋል።

ሰራዊቱ የሚገጥሙትን ፈተናዎች በቁርጠኝነት በማለፍ ድል እያስመዘገበ መሆኑንም ሚኒስትሩ ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ህዝቦች ለመከላከያ ሰራዊት አያደረጉ ያለው ድጋፍ ለሀገራቸውና ለሰራዊቱ ያላቸውን ክብርና ፍቅር የሚያሳይ ነው ያሉት ሚኒስትሩ፥ ከሰራዊቱ ጎን በመቆም አለኝታነታቸውን ላረጋገጡት ሁሉ ምስጋናቸውን አቅርቧል።

በሙክታር ጠሃ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.