Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ ባለሥልጣናት በኡጋንዳ ከሕወሐት ጋር በሽምግልና ውይይቶች ላይ ይሳተፋሉ በሚል የተሰራጨው መረጃ የተሳሳተ መሆኑ ተገለፀ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 7፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢትዮጵያ ባለሥልጣናት በኡጋንዳ ከሕወሓት ጋር በሽምግልና ውይይቶች ላይ ይሳተፋሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ በተለያዩ የዜና አውታሮች የቀረበው መረጃ የተሳሳተ እና በአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጅ ግብረ ኃይል ያልተረጋገጠ መሆኑን ጠቅሷል፡፡

የፌደራል መንግሥት በትግራይ ክልል የሕግ የበላይነትን ለማስከበር በቁርጠኝነት እየሠራ ይገኛልም ብሏል፡፡

የሚዲያ አካላት እንደ መሠረታዊ የጋዜጠኝነት አሠራር የኢትዮጵያን የሕግ የበላይነት የሚመለከቱ ጥያቄዎችን ሁልጊዜ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ግብረ ኃይል ፕሬስ ሴክሬታሪያት በኩል እንዲያረጋግጡ ጥሪ እናቀርባለንም ነው ያለው ፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.