የሀገር ውስጥ ዜና

የአፍሪካ ኢንዱስትሪያላይዜሽን ሳምንት በአዲስ አበባ መካሄድ ጀመረ

By Tibebu Kebede

November 16, 2020

አዲስ አበባ፣ ህዳር 7፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ለአራት ቀናት የሚቆየው የአፍሪካ ኢንዱስትሪያላይዜሽን ሳምንት በአዲስ አበባ መካሄድ ጀመረ።

በቪዲዮ ኮንፈረንስ የሚካሄደው የአፍሪካ ኢንዱስትሪያላይዜሽን ሳምንት “ሁሉን አቀፍና ዘላቂነት ያለው ኢንዱስትሪያላይዜሽን በአህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጠና” በሚል መሪ ቃል ነው እየተካሄደ የሚገኘው፡፡

ዝግጅቱ በአህጉሪቱ በተለያዩ ኢንዱስትሪ ዘርፎች የተሰማሩ አካላትን በአንድ ለማገናኘት ያለመ መሆኑን ከአፍካ ህብረት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

እንዲሁም አፍሪካ ወደ ኢንዱስትራላይዜሽን በምታደርገው ጉዞ ላይ ግንዛቤ ለመፍጠር ፣ ተግባራዊ እየተደረጉ ስለሚገኙ ጉዳዮች ለማሳወቅ እና አፍሪካ ያጋጠማት መዋቅራዊ የለውጥ ተግዳሮቶች ላይ ለመምከርም ግብ አድርጎ የተነሳ ዝግጅት ነው።

በተጨማሪም የአፍሪካ ኢንዱስትሪያላይዜሽን ሳምንቱ ለዘርፉ የተሻለ ልምድ ካላቸው ልምድ ለማግኘት እንደሚያስችል ተጠቁሟል።