Fana: At a Speed of Life!

በአቶ ደመቀ መኮንን የተመራ የልዑካን ቡድን  በምስራቅ አፍሪካ ሀገራት ጉብኝት እያካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ህዳር 7፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን የተመራ የልዑካን ቡድን በምስራቅ አፍሪካ ሀገራት ጉብኝት እያካሄደ ነው።
በመከላከያ ሰራዊት ላይ ጥቃት በመክፈት የሀገር ክህደት የፈፀመውና ተከታታይ የህገ መንግሰት ጥሰቶችን ሲፈፅም የከረመው የአክራሪውን የህወሃት ፅንፈኛ ቡድን መንግስት ለህግ ለማቅረብ፣ የህግ የበላይነትን የማስፈን ዘመቻ በመካሄድ ላይ መሆኑ ይታወቃል።
ይኸው ዘመቻ የውስጥ ጉዳያችንን በራሳችን አቅም መልክ ለማስያዝ የሚካሄድ በመሆኑና አክራሪው ሃይል በህግ ስር ከመሆኑ በፊት ምንም አይነት የውጭ ሃይል እንቅስቃሴ ስርዓት አልበኝነትን በማንገስ የሀገራችንን ሰላም የማደፍረስ ውጤት የሚያስከትል መሆኑን መንግስት አቋሙን ግልፅ አድርጓል።
ይህንኑ አቋም በማስረዳት የቀጠናው አገራት መንግስት የጀመረውን ህግና ህገ መንግስት የማጽናት ጥረት እንዲደግፉ ለማስቻል የጠቅላይ ሚኒስትሩን መልዕክት የያዘና በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን የተመራ የልዑካን ቡድን ወደ ተለያዩ የቀጠናው አገራት ጉብኝት ጀምሯል።
ጉብኝቱ ከስድስት በላይ አገራትን የሚሸፍን መሆኑ ታውቋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ዩጋንዳ ለማሸማገል እንዳሰበችና ለዚሁ ሲባል የልዑካን ቡድን እንደሚጓዝ የሚያትትና በኢትዮጵያም ሆነ በዩጋንዳ ያልታሰበና ተቀባይነት የሌለው የሐሰት መረጃ በፅንፈኛው ቡድን ተፈብርኮ በአንዳንድ የመገናኛ ብዙሃን በመሰራጨት ላይ እንዳለ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.