Fana: At a Speed of Life!

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለሰሜን ዕዝ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ቤተሰቦች እና ልጆች የትምህርት እና ጤና እንክብካቤ እንደሚያደርግ አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 7፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አበቤ የህወሓት የጥፋት ቡድን በሰሜን ዕዝ በሚገኙ የሀገር መከላከያ ሰራዊት ጥቃት ለደረሰባቸው የሰራዊቱ አባላት ልጆች የከተማ አስተዳደሩ የትምህርት እና ጤና እንክብካቤ እንደሚያደርግ ገለጹ፡፡

ምክትል ከንቲባዋ “ከባንዳ ጋር ተባብረን ክህደት አንፈጽምም” ብለው ህይወታቸውን ለሰጡ ለጀግናው መከላከያ ሰራዊት ቤተሰቦች እና ልጆቻቸው የከተማ አስተዳደሩ ከህዝቡ ጋር በመሆን ምንም ሳይጎድልባቸው ተንከባቦ እንደሚያኖራቸው ልጆቻቸውንም እንደሚያስተምር ነው የተናገሩት፡፡

የሀገር እና የአፍሪካ ኩራት ለሆነው የመከላከያ ሠራዊት የህይወት፣ የሃብት እና የሙያ ድጋፍ ላበረከቱ ሁሉ ክብር እና ምስጋናዬ የላቀ ነው ማለታቸውን ከአዲስ አበባ ከተማ ፕሬስ ሴክሬተርያት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.