የሀገር ውስጥ ዜና

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለሰሜን ዕዝ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ቤተሰቦች እና ልጆች የትምህርት እና ጤና እንክብካቤ እንደሚያደርግ አስታወቀ

By Abrham Fekede

November 16, 2020

አዲስ አበባ፣ ህዳር 7፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አበቤ የህወሓት የጥፋት ቡድን በሰሜን ዕዝ በሚገኙ የሀገር መከላከያ ሰራዊት ጥቃት ለደረሰባቸው የሰራዊቱ አባላት ልጆች የከተማ አስተዳደሩ የትምህርት እና ጤና እንክብካቤ እንደሚያደርግ ገለጹ፡፡

ምክትል ከንቲባዋ “ከባንዳ ጋር ተባብረን ክህደት አንፈጽምም” ብለው ህይወታቸውን ለሰጡ ለጀግናው መከላከያ ሰራዊት ቤተሰቦች እና ልጆቻቸው የከተማ አስተዳደሩ ከህዝቡ ጋር በመሆን ምንም ሳይጎድልባቸው ተንከባቦ እንደሚያኖራቸው ልጆቻቸውንም እንደሚያስተምር ነው የተናገሩት፡፡