Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ኢንጅነር ሀብታሙ ከዓለም ባንክ የኢትዮጵያ ዳይሬክተር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 7፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ኢንጅነር ሀብታሙ ተገኝ ከዓለም ባንክ የኢትዮጵያ ዳይሬክተር ኦስማን ዲዮን ጋር ተወያዩ።

በውይይታቸው ኢትዮጵያ እና የዓለም ባንክ በትብብር ወሳኝ የሆኑ የመንገድ እና የሃይል መሰረተ ልማት ስራዎችን የበለጠ ማዘመን በሚችሉበት አግባብ ላይ ተወያይተዋል፡፡

የመንገድ ሀብት አስተዳደር ልምድን እና ቀጠናዊ ትብብርን ማሻሻል በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ትኩረት አድርገውም ተወያይተዋል።

የዓለም ባንክ ከፈረንጆቹ 1991 ጀምሮ በኢትዮጵያ የመሰረተ ልማት ክፍተትን ለመሙላት ከ2 ቢሊየን ዶላር በላይ ፈሰስ ማድረጉን ገልፀዋል።

ይህም በኢትዮጵያ የመንገዶችን የጥራት ደረጃ እና የመንገድ ትስስር ዝርጋታ መጨመሩንም የዓለም ባንክ በኢትዮጵያ ያወጣው መረጃ ያመላክታል።

በመሆኑም የኢትዮጵያ የመንገድ ሽፋን በ1991 ከነበረበት 20 ሺህ ኪሎ ሜትር በ2020 ወደ 144 ሺህ መድረሱ ተጠቁሟል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.