የሀገር ውስጥ ዜና

ዶክተር ሙላቱ ተሾመ ከሳዑዲ ዓረቢያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር ተወያዩ

By Tibebu Kebede

December 30, 2019

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 20 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዴሪ የቀድሞው ፕሬዚዳንት ዶክተር ሙላቱ ተሾመ ከሳዑዲ ዓረቢያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፈይሰል ቢን ፋርሃን ቢን አብዱላህ ጋር ተወያዩ።

በውይይታቸውም በሁለቱ ሃገራት የሁለትዮሽ ግንኙነትና በጋራ ጉዳዮች ላይ መክረዋል።

ዶክተር ሙላቱ ተሾመ በትናንትናው እለት ነበር ወደ ሳዑዲ ዓረቢያ ያቀኑት።

ሪያድ ንጉስ ካሊድ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱም በሳዑዲ አረቢያ የአፍሪካ ጉዳዮች ሚኒስትር ፕሮፌሰር አህመድ ቢን አብዱላዚዝ ቃታን አቀባበል ተደርጎላቸዋል።

ምንጭ፦ spa.gov.sa