Fana: At a Speed of Life!

በአሜሪካ ቴክሳስ ቤተክርስቲያን ውስጥ በተከፈተ ተኩስ የሁለት ሰዎች ሕይወት አለፈ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 20፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአሜሪካ ቴክሳስ ቤተክርስቲያን ውስጥ በተከፈተ ተኩስ የሁለት ሰዎች ሕይወት አለፈ።

ጥቃት አድራሹ ሁለት ምዕመናንን ከገደለ በኋላ በተከፈተ የአጸፋ ተኩስ መገደሉን ፖሊስ አስታውቋል።

በወቅቱ ግለሰቡ ጥቃቱን የፈጸመበትን ምክንያት እያጣራ መሆኑንም ገልጿል።

ጥቃቱ በጠዋቱ የአገልግሎት ሰዓት ላይ መፈጸሙንም ነው ፖሊስ የገለጸው።

የቴክሳስ ገዥ ግሬግ አቦት የአምልኮ ስፍራዎች የተቀደሱ መሆናቸውን ጠቅሰው ተጨማሪ ህይወት እንዳይጠፋ ጥቃት አድራሹ ላይ እርምጃ ለወሰዱ የቤተክርስቲያኗ አባላት ምስጋና አቅርበዋል።

ባለፈው መስከረም ወር በቴክሳስ ፈቃድ ያላቸው ግለሰቦች በአምልኮ ስፍራዎች መሳሪያ እንዲታጠቁ የሚያስችል አዲስ ህግ ተግባራዊ ተደርጓል።

በቴክሳስ ባለፈው ነሃሴ ወር በተለያየ ቦታ በተፈጸሙ ሁለት ተመሳሳይ ጥቃቶች 29 ሰዎች መገደላቸው የሚታወስ ነው።

ምንጭ፦ ቢቢሲ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.