የሀገር ውስጥ ዜና

ህወሓት ከነባራዊ ሁኔታ በተቃራኒ ሀሰተኛ መረጃዎችን እየነዛ በመሆኑ በተጨባጭ መሬት ላይ ያለውን ነገር መገንዘብ ያስፈልጋል – አምባሳደር ሬድዋን

By Tibebu Kebede

November 16, 2020

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 7 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ለሚገኙ ዓለም አቀፍ ሚዲያ ተቋማት ተወካዮች በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ማብራሪያ እየተሰጠ ነው፡፡

ማብራሪያውን እየሰጡ የሚገኙት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የመረጃ ፍሰት ቃል አቀባይ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን የሚዲያ ተቋማቱ በህወሓት ሀሰተኛ የፕሮፖጋንዳ መረጃ እንዳይወዛገቡ አሳስበዋል።

ከነባራዊ ሁኔታ በተቃራኒ ሀሰተኛ መረጃዎችን ህወሓት እየነዛ መሆኑን በመግለፅ በተጨባጭ መሬት ላይ ያለውን ነገር መገንዘብ ያስፈልጋል ብለዋል።

ለሰብዓዊ ቀውስ ምላሽ የሚሰጥ እና የሚያስተባብር የከፍተኛ ባለስልጣናት ኮሚቴ መዋቅሩንም አምባሳደር ሬድዋን ገልፀዋል።

አምባሳደሩ ኮሚቴው በአካባቢው ተሰማርቶ ምላሽ መስጠት የሚያስችል መረጃ እያሰባሰበ እንደሆነ መናገራቸውን ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መረጃ ማጣሪያ የገኘነው መረጃ ያመላክታል።