Fana: At a Speed of Life!

በአቶ ደመቀ መኮንን የተመራ የልዑካን ቡድን ናይሮቢ ገባ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 7፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን የተመራ የልዑካን ቡድን ናይሮቢ ገብቷል።
 
በመከላከያ ሰራዊት ላይ ጥቃት በመክፈት የሀገር ክህደት የፈፀመውና ተከታታይ የህገ መንግሰት ጥሰቶችን ሲፈፅም የከረመው የአክራሪውን የህወሃት ፅንፈኛ ቡድን መንግስት ለህግ ለማቅረብ፣ የህግ የበላይነትን የማስፈን ዘመቻ በመካሄድ ላይ መሆኑ ይታወቃል።
 
ይኸው ዘመቻ የውስጥ ጉዳይን በራስ አቅም መልክ ለማስያዝ የሚካሄድ በመሆኑና አክራሪው ሃይል በህግ ስር ከመሆኑ በፊት ምንም አይነት የውጭ ሃይል እንቅስቃሴ ስርዓት አልበኝነትን በማንገስ የሀገራችንን ሰላም የማደፍረስ ውጤት የሚያስከትል መሆኑን መንግስት አቋሙን ግልፅ አድርጓል።
 
ይህንኑ አቋም በማስረዳት የቀጠናው አገራት መንግስት የጀመረውን ህግና ህገ መንግስት የማጽናት ጥረት እንዲደግፉ ለማስቻል የጠቅላይ ሚኒስትሩን መልዕክት የያዘና በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን የተመራ የልዑካን ቡድን ከኬንያው ፕሬዝደንት ኡሁሩ ኬንያታ ጋር እንደሚወያይ በኬንያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ አስታውቋል።
 
 
አቶ ደመቀ መኮንን ዛሬ ከኡጋንዳው ፕሬዝደንት ዮዌሪ ሙሴቬኒ ጋር መወያየታቸው ይታወሳል።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.