Fana: At a Speed of Life!

በ24 ሰዓታት 336 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ሲገኝባቸው የ12 ሰዎች ህይወት አልፏል

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 7፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ በተደረገው 4 ሺህ 213 የላብራቶሪ ምርመራ 336 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።

በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 103 ሺህ 56 መድረሱንም ሚኒስቴሩ ያወጣው እለታዊ መረጃ ያመለክታል።

ከዚህ ባለፈ የ12 ሰዎች ህይወት በቫይረሱ ምክንያት ያለፈ ሲሆን፥ በአጠቃላይ በኢትዮጵያ በቫይረሱ ምክንያት ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር 1 ሺህ 581 መድረሱንም አመላክተዋል።

በሌላ መልኩ በትናንትናው እለት 264 ሰዎች ከኮሮና ቫይረሱ ያገገሙ ሲሆን፥ በአጠቃላይ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 64 ሺህ 130 መድረሱም ተገልጿል።

ከቫይረሱ ጋር በተያያዘ እስካሁን ለ1 ሚሊየን 566 ሺህ 221 ሰዎች ምርመራ የተደረገ ሲሆን፥ በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 103 ሺህ 56 ደርሷል።

አሁን ላይ ቫይረሱ ያለባቸው ሰዎች ቁጥር 37 ሺህ 343 ሲሆን፥ ከእነዚህም ውስጥ 308 ሰዎች በጽኑ የታመሙ መሆናቸውንም የጤና ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.