መንግስት ወደ ጎረቤት ሀገራት የሚሰደዱ ዜጎችን ለመቀበል ዝግጁ ነው-ጠ/ሚ ዐቢይ
አዲስ አበባ ፣ ህዳር 8 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢትዮጵያ መንግስት ወደ ጎረቤት ሀገራት የሚሰደዱ ወገኖችን ለመቀበል እና ወደ ቀዬአቸው ለመመለስ ዝግጁ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ገለፁ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስት ዐቢይ በትዊተር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት÷የተሰደዱ ንፁሀን ዜጎችን ንብረታቸውን ለመጠበቅ ፣ በኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት የሰብአዊ ድጋፍ ለማቅረብ እና ሲመለሱም ሰላማቸውን ለማስጠበቅ ዝግጁ መሆኑን ገልጸዋል።
#FBC
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።