ስፓርት

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ክለብ የአትሌቲክስ አሰልጣኝ ተፈሪ መኮንን ከዚህ አለም በሞት ተለዩ

By Meseret Awoke

November 17, 2020

አዲስ አበባ፣ ህዳር 8፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) አንጋፋው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ክለብ የአትሌቲክስ አሰልጣኝ ተፈሪ መኮንን ከዚህ አለም በሞት ተለዩ፡፡

አሰልጣኝ ተፈሪ መኮንን በአትዮጵያ ንግድ ባንክ አትሌቲክስ ክለብ፣ በብሄራዊ ቡድንና በተለያዩ ክለቦች በአሰልጣኝነት ውጤታማ የስራ የሰሩና ለበርካታ ውጤታማ አትሌቶች መፍራት ድርሻ የነበራቸው አሰልጣኝ እንደነበሩ ተገልጿል፡፡

በአሰልጣኙ ድንገተኛ ህልፈት የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የተሰማውን ጥልቅ ሃዘን እየገለፀ ለቤተሰቦቻቸው፣ ለወዳጅ ዘመዶቻቸውና ለክለቡ አባላት በሙሉ ልባዊ መፅናናት መመኘቱን ከፌዴሬሽኑ የፌስቡክ ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።