የህወሓት ቡድን ለሰራው ግፍ የእጁን ማግኘት አለበት – አቶ ሽመልስ አብዲሳ
አዲስ አበባ፣ ህዳር 8፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) የህወሓት ቡድን ለሰራው ግፍ የእጁን ማግኘት እንዳለበት የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ ገለጹ፡፡
አቶ ሽመልስ አብዲሳ ዛሬ በተከበረው “ለመከላከያ ሠራዊት ክብር እቆማለሁ ” ፕሮግራም ላይ ባሰሙት ንግግር ስግብግቡ የህወሓት ጁንታ ባለፉት አመታት በኦሮሞ ህዝብ ላይም ሆነ እንደ ሀገር ላደረሳቸው ዘግናኝ የሆኑ ግፎች የእጁን ማግኘት እንዳለበት አንስተዋል።
የህወሓት ቡድን በጀግናው የሀገር መከላከያ ሠራዊት ላይ ያደረሰው ጥቃት የሚያሳዝንና መቼም ይቅር የማይባል መሆኑንም ተናግረዋል።
አቶ ሽመልስ አብዲሳ እንዳሉት አረመኔው የህወሓት ቡድን ከዚህ የውድቀት ጫፍ ላይ የደረሰውም በብዙ ሺህ ኢትዮጵያውያን ላይ ባደረሰው በደል ነው።
ለሀገር መከላከያ የሚደረገው ድጋፍ ተጠናክሮ ይቀጥላል ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ፥ የቡድኑ መወገድ ለኢትዮጵያውያን ትልቅ እረፍት ነው ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።