የሀገር ውስጥ ዜና

“ለሀገር መከላከያ ክብር እቆማለሁ” መርሃ ግብር  በደቡብ ክልል ተከበረ

By Meseret Demissu

November 17, 2020

አዲስ አበባ፣ ህዳር 8 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ)”ለሀገር መከላከያ ክብር እቆማለሁ” መርሃ ግብር በደቡብ ክልል ተካሄደ፡፡

ፕሮግራሙ የደቡብ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ እርስቱ ይርዳና ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት ነው የተካሄደው።

በፕሮግራሙ ላይ የደቡብ ክልል ፖሊስ፣ ልዩ ሃይልና፣ የመንግስት ሰራተኞችና አመራሮች የተገኙ ሲሆን ግንባር ላይ ለሀገር ሉዓላዊነትና የህግ የበላይነት እየተዋደቀ ለሚገኘው የሀገር መከላከያ ሰራዊት ክብር የክልሉ ፖሊስ ማርቺንግ ባንድ የሰልፍ  ትርኢት ማሳየቱን ከክልሉ ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።