ለሀገር መከላከያ ክብር እቆማለሁ” መርሃ ግብር በአማራ ክልል ተካሄደ
አዲስ አበባ፣ ህዳር 8 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) “ለሀገር መከላከያ ክብር እቆማለሁ” መርሃ ግብር በአማራ ክልል ተካሄደ፡፡
መርሃ ግብሩ በባህር ዳር እና ጎንደርን ጨምሮ በክልሉ የተለያዩ ከተሞች ነው የተካሄደው፡፡
በመርሃ ግብሩ ላይ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ አገኘሁ ተሻገርን ጨምሮ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች፣ የመከላከያና የክልሉ ልዩ ሃይል አመራሮች እና አባላት ተገኝተዋል፡፡
የመርሃ ግብሩ ተሳታፊዎች ለአንድ ደቂቃ ቀኝ እጃቸውን ግራ ደረታቸው ላይ በማድረግ ለመከላከያ ሠራዊት፣ ለአማራ ልዩ ሃይልና ሚሊሻ አባላት ያላቸውን ክብር አሳይተዋል፡፡