“ለሀገር መከላከያ ክብር እቆማለሁ” መርሃ ግብር በአፋር ክልል ተካሄደ
አዲስ አበባ፣ ህዳር 8፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) “ለሀገር መከላከያ ክብር እቆማለሁ” መርሃ ግብር በአፋር ክልል በተለያዩ አካባቢዎች ተካሄደ።
በሰመራ ከተማ በተካሄደው መርሃ ግብር ላይ የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አወል አርባን ጨምሮ ሌሎችም ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።
“ለሀገር መከላከያ ክብር እቆማለሁ” መርሃ ግብሩ ከሰመራ ከተማ በተጨማሪ በሌሎች የክልሉ አካባቢዎች መካሄዱን ከክልሉ የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
በመርሃ ግብሩ ላይ የተሳተፉ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ለሀገር ለመከላከያ ሰራዊት ያላቸውን ክብር በመግለፅ ከሰራዊቱ ጎን መሆናቸውን አረጋግጠዋል።