የሀገር ውስጥ ዜና

በአብዬ የሚገኙ የስምንተኛ ዙር ሁለገብ ሎጅስቲክስ ሰላም አስከባሪ የሰራዊት አባላት “ለሀገር መከላከያ ሰራዊት ክብር እቆማለሁ” ሲሉ ጓዶቻቸውን አስበዋል

By Meseret Awoke

November 17, 2020

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 8፣ 2013 (ኤፍቢሲ) በአብዬ የሚገኙ የስምንተኛ ዙር ሁለገብ ሎጅስቲክ ሰላም አስከባሪ የሰራዊት አባላት “ለሀገር መከላከያ ሰራዊት ክብር እቆማለሁ” ሲሉ ጓዶቻቸውን ማሰባቸው ተገለጸ።

በሀገር አቀፍ ደረጃ ዛሬ መላው ህዝብ ለሰራዊቱ የሰጠውን ክብር ለመደገፍ፣ ህግን ለማስከበርና የህልውና ዘመቻውን በጀግንነት እየፈፀሙ የሚገኙ አባላትን ለአንድ ደቂቃ የሻምበሉ አባላት ማሰባቸው ተነግሯል።

ስግብግቡ የህውሓት ጁንታ በሰሜን ዕዝ የሰራዊት አባላት ላይ የፈፀመው ኢ-ሰብዓዊ ጭፍጨፋ የተወገዘ ሲሆን ፣ ለሀገራቸው እና ለህዝባቸው ክብር ሲሉ በጀግንነት የተዋደቁ የሰራዊቱ አባላት ታሪክና ህዝብ አይረሳቸውም መባሉን ከኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።