የሀገር ውስጥ ዜና

“የኢትዮጵያ መንግሥት ከደቡብ ሱዳን የጦር ድጋፍ እንዲደረግለት በደብዳቤ ጠይቋል ተብሎ የሀሰት ዜና ተሰራጭቷል­- የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የመረጃ ማጣሪያ

By Tibebu Kebede

November 17, 2020

አዲስ አበባ፣ ህዳር 8፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) “የኢትዮጵያ መንግሥት ከደቡብ ሱዳን የጦር ድጋፍ እንዲደረግለት በደብዳቤ ጠይቋል” ተብሎ የሀሰት ዜና መሰራጨቱን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የመረጃ ማጣሪያ ገለፀ።

እንዲህ ያሉ የፈጠራ ዜናዎች፣ የሀገር ውስጥ ጉዳይን ቀጣናዊ ገጽታ ያለው አስመስሎ ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ለማቅረብ በአጥፊዎቹ አካላት የሚደረግ ጥረት መሆኑንም አስታውቋል።

ሁሉም ሰው ይህን የመሰሉ የሀሰት ዜናዎችን ባለማጋራት፣ የተሳሳተ መረጃን ከማሰራጨት እንዲቆጠቡ ሲልም የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የመረጃ ማጣሪያ ጥሪውን አቅርቧል።