Fana: At a Speed of Life!

ጠ/ሚ ዐቢይ “ለሀገር መከላከያ ክብር እቆማለሁ” መርሃ ግብርን ላዘጋጁና ለተሳተፉ ምስጋና አቀረቡ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 8፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ “ለሀገር መከላከያ ክብር እቆማለሁ” መርሃ ግብርን ላዘጋጁና ለተሳተፉ ሁሉ ምስጋና አቀረቡ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በፌስቡክ ገፃቸው ባወጡት መረጃ፥ “በሀገሬ ሕዝብና በኢትዮጵያዊነቴ ኮራሁ” ብለዋል።
“ለመከላከያ ሠራዊት ክብር እቆማለሁ” በሚል መሪ ቃል ዛሬ ኢትዮጵያውያን ለሠራዊቱ ያላቸውን ድጋፍ ማሳየታቸውንም አስታውሰዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በመልእክታቸው አክለውም፥ “መርሐ ግብሩን ላዘጋጁ የኪነ ጥበብ ባለሞያዎችና ለተሳተፉ ሁሉ ምስጋናዬን አቀርባለሁ” ብለዋል።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.