የሀገር ውስጥ ዜና

የሕወሓት ጁንታ የትግራይ መሠረተ ልማቶችን እያፈረሰ ነው – አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መረጃ ማጣሪያ

By Tibebu Kebede

November 17, 2020

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 8 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የሕወሓት ጁንታ የትግራይ መሠረተ ልማቶችን እያፈረሰ መሆኑን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መረጃ ማጣሪያ አስታወቀ።

የመከላከያ ሠራዊት ወደፊት መገሥገሡ ያስጨነቀው ጁንታ፣ በሁሉም አቅጣጫ ወደ መቐለ በሚወስዱት መንገዶች ላይ የሚገኙ አራት ድልድዮች ማፍረሱንም ነው ያስታወቀው።

የተማመነባቸው ከባድ ምሽጎቹ ፈራርሰው፣ በሽሬ መንገድ የደረሰበት ሽንፈት ያንገበገበው ጁንታ፣ በሽሬና በአክሱም መካከል የሚገኘውን አስፓልት በግሬደር ቆፍሮ ወደ ጉድጓድነት ቀይሮታልም ነው ያለው።

የሕወሓት ጁንታ እስከዛሬ ከፈጸማቸው ወንጀሎች በተጨማሪ ባወደማቸው መሠረተ ልማቶች በቅርቡ ይጠይቅባቸዋልም ብሏል።