Fana: At a Speed of Life!

ትራምፕ በምርጫ ጉዳይ ላይ የደህንነት ኃላፊ የነበሩትን ግለሰብ አሰናበቱ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 9፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በምርጫ ጉዳዮች ላይ የደህንነት ኃላፊያቸውን ማሰናበታቸውን አስታወቁ፡፡

ከኃላፊነት የተባረሩት ክሪስ ክሬብስ የበይነ መረብ ደህንነትና የጸጥታው ኤጀንሲ የመሰረተልማት ኃላፊ ነበሩ፡፡

ትራምፕ ኃላፊውን ያባረሩት ምርጫው ተጭበርብሯል በሚል የሚያቀርቡትን ክስ ውድቅ በማድረጋቸው ነው ተብሏል፡፡

ፕሬዚዳንቱ እስካሁን በምርጫ መሸነፋቸውን ያላመኑ ሲሆን በአንጻሩ ክሪስ ክሬብስን ጨምሮ ምርጫውን የሚመሩ ኃላፊዎች በአሜሪካ ታሪክ ደህንነቱ የተጠበቀ ምርጫ እንደነበር ይፋ አድርገዋል፡፡

የኃላፊው መባረር በዴሞክራቶች ዘንድ ቁጣን የቀሰቀሰ ሲሆን የጆ ባይደን ቃልአቀባይ ኃላፊው የሀገሪቱን የምርጫ ደህንነት ማረጋገጥ በመቻላቸው ምስጋና ሊቸራቸው ይገባል ብለዋል፡፡

ከምርጫ ኃላፊው በተጨማሪ ባለፈው ሳምንት የመከላከያ ሚኒስትሩ ማርክ ኤስፐርን ከስልጣን አንስተዋል፡፡

ፕሬዚዳንቱ ስልጣናቸውን ለቀጣዩ ፕሬዚዳንት ከማስረከባቸው በፊት የኤፍ ቢ አይና የሲ አይ ኤ ዳይሬክተሮችንም ከስልጣን ሊያነሱ ይችላሉ እየተባለ ነው፡፡

 

ምንጭ፡-ቢቢሲ

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.